ጉልብት እንደሌለው
እራሱ እያወቀው
የሱ ለርሱ ብቻ ወቅቱ ስለሆነ
በነነ ገነነ
ላይሆን ደርቆ ቀልጦ የሚጠበስ እሸት
ታፍሶ ተጨልፎ ወጥ ላይሰራበት
ተቆፍሮ ታርሶ ሩዝ ላይበቅልበት
እያብለጨለጨ ወራት አለፈበት
እኛም አወቅንና የበረዶን ጉልበት
ዘዴ ዘየድንበት
ተንሸራተትንበት ተንከባለልበት
ጨብጠን በትነን ተደባድብንበት
ውዱም ውዳን ይዞ
እንጨት ተመርኩዞ
ብረት ተመርኮዞ
ጀመሩበት ጉዞ
ባይሞቅም ባይደላም
ነገሩ አያስጠላም
ውዲት ከውዱ ጋር ተነጋገሩና ምክር አመጡበት
በረዶን ሊሞቁት ጎጆ ቀለሱበት።