Monday, March 15, 2010

ወፍና ጠጠር

ቀኑ መሽቶ ነግቶ
ሌሊቱ በትግል ወጦ ተጎትቶ
ጧት ማለዳ ላይ
ዝማሬን አውጥቼ ሆኜ ጎጄ ላይ
የሚበላ ነገር አምሮኝ ስንዴ ነገር
ወረድኩ ባገኝ ብየ ተቀላቅሎ ካፈር
የዚህ ሀገር ነገር
ጠፍቶ ይሁን አፈር
ወይም ተደብቆ
በኖ በኖ ተበትኖ ደቆ
ወይ እግር በዝቶበት ሆኖ ይሁን ኮረት
አላውቅም እንጃለት
ብቻ እራበኝና አንጀቴ ብሶበት
ስንዴ መስሎኝ ለኔ ጠጠሩን በላሁት
ኮረቱን ለቀምኩት

1 comment:

  1. Hello man! You write really nice poems. Yenuro ashkilawa beza meselegn demo. Ayzon sanalf ken yalfal.

    ReplyDelete